ኢዮብ 27:9-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. በውኑ መከራ በገጠመው ጊዜ፣እግዚአብሔር ጩኸቱን ይሰማልን?

10. ሁሉን በሚችል አምላክ ደስ ይለዋልን?ዘወትርስ እግዚአብሔርን ይጠራልን?

11. “ስለ እግዚአብሔር ክንድ አስተምራችኋለሁ፤የሁሉን ቻዩንም አምላክ ዕቅድ አልሸሽግም።

12. ሁላችሁ ይህን አይታችኋል፤ታዲያ፣ ይህ ከንቱ ንግግር ምንድን ነው?

13. “እግዚአብሔር ለክፉው የመደበው ዕድል ፈንታ፣ግፈኛም ሁሉን ከሚችል አምላክ የሚቀበለው ቅርስ ይህ ነው፦

ኢዮብ 27