3. እግዚአብሔርም ሰይጣንን፣ “አገልጋዬን ኢዮብን ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ነቀፋ የሌለበት፣ ቅን፣ እግዚአብሔርን የሚፈራና ከክፋት የራቀ ሰው የለም፤ ያለ ምክንያት እንዳጠፋው ብትወተውተኝም፣ ይኸው ፍጹምነቱን እንደ ጠበቀ ነው” አለው።
4. ሰይጣንም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ ‘ቍርበት ስለ ቍርበት ነው’ እንዲሉ ሰው ለሕይወቱ ሲል ያለውን ሁሉ ይሰጣል፤
5. እስቲ እጅህን ዘርግተህ ዐጥንቱንና ሥጋውን ዳስ፤ በእርግጥ ፊት ለፊት ይሰድብሃል።”
6. እግዚአብሔርም ሰይጣንን፣ “እነሆ፤ እርሱ በእጅህ ነው፤ ሕይወቱን ግን እንዳትነካ” አለው።
7. ከዚህ በኋላ ሰይጣን ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ሄደ፤ ኢዮብንም ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ጠጒሩ በክፉ ቍስል መታው።
8. ኢዮብም ገላውን ለማከክ ገል ወሰደ፤ በዐመድም ላይ ተቀመጠ።
9. ሚስቱም፣ “አሁንም ታማኝነትህን አልተውህምን? ይልቁን እግዚአብሔርን ርገምና ሙት!” አለችው።
10. እርሱም፣ “አነጋገርሽ እንደማታስተውል ሴት ነው፤ መልካሙን ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ተቀበልን፣ ክፉውንስ አንቀበልምን? አላት።”በዚህ ሁሉ፣ ኢዮብ በንግግሩ አልበደለም።