ኢሳይያስ 53:11-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ከነፍሱ ሥቃይ በኋላ፣የሕይወት ብርሃን ያያል፤ ደስም ይለዋል፤ጻድቅ ባሪያዬ በዕውቀቱ ብዙዎቹን ያጸድቃል፤መተላለፋቸውንም ይሸከማል።

12. ስለዚህ ድርሻውን ከታላላቆች ጋር እሰጠዋለሁ፤ምርኮውን ከኀያላን ጋር ይካፈላል፤እስከ ሞት ድረስ ሕይወቱን አሳልፎ በመስጠቱ፣ከክፉ አድራጊዎችም ጋር በመቈጠሩ፣የብዙዎችን ኀጢአት ተሸከመ፤ስለ ዐመፀኞችም ማለደ።

ኢሳይያስ 53