ናሆም 2:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ነነዌ ሆይ፤ አጥቂ መጥቶብሻል፤ምሽግሽን ጠብቂ፤መንገድሽን ሰልዪ፤ወገብሽን ታጠቂ፤ኀይልሽን ሁሉ አሰባስቢ።

2. አጥፊዎች ባድማ ቢያደርጓቸውም፣የወይን ተክል ቦታቸውን ቢያጠፉባቸውም፣እንደ እስራኤል ክብር ሁሉ፣ እግዚአብሔር የያዕቆብንም ክብር ይመልሳል።

3. የወታደሮቹ ጋሻ ቀይ ነው፤ተዋጊዎቹ ቀይ ልብስ ለብሰዋል፤ዝግጁ በሆኑበት ቀን፣የሠረገሎቹ ብረት ያብረቀርቃል፤የጦሩ ዘንግ ይወዛወዛል።

ናሆም 2