ማሕልየ መሓልይ 4:10-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. እኅቴ ሙሽራዬ፣ ፍቅርሽ እንዴት ደስ ያሰኛል!ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ ምንኛየሚያረካ ነው፤የሽቱሽም መዐዛ ከቅመም ሁሉ ይልቅ የቱን ያህል ይበልጥ!

11. ሙሽራዬ ሆይ፤ ከንፈሮችሽ የማር ወለላ ያንጠባጥባሉ፤ከአንደበትሽም ወተትና ማርይፈልቃል፤የልብስሽም መዐዛ እንደ ሊባኖስ ሽታ ነው።

12. እኅቴ ሙሽራዬ፤ የታጠረ የአትክልት ቦታ፣ዙሪያውን የተከበበ ምንጭ፣ የታተመም ፏፏቴ ነሽ።

13. ተክልሽ ሮማን፣ምርጥ ፍሬዎች፣ሄናና ናርዶስ ያሉበት ነው።

14. እንዲሁም ናርዶስና ቀጋ፣ጠጅ ሣርና ቀረፋ፣የተለያዩ የዕጣን ዛፎች፣ከርቤና እሬት፣ምርጥ ቅመሞች ሁሉ አሉበት።

15. አንቺ የአትክልት ቦታ ፏፏቴ፣ከሊባኖስ የሚወርድ፣የፈሳሽ ውሃ ጒድጓድ ነሽ።

16. የሰሜን ነፋስ ሆይ፤ ንቃ፤የደቡብም ነፋስ ሆይ፤ ና!መዐዛው ያውድ ዘንድ፣በአትክልት ቦታዬ ላይ ንፈስ፤ውዴ ወደ አትክልት ቦታው ይግባ፤ምርጥ ፍሬዎቹንም ይብላ።

ማሕልየ መሓልይ 4