ሐዋርያት ሥራ 26:30-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

30. ከዚህ በኋላ ንጉሡም፣ አገረ ገዡም፣ በርኒቄም፣ ከእነርሱ ጋር የተቀመጡትም ተነሡ፤

31. ወጥተውም ሲሄዱ፣ “ይህ ሰው እንኳን ለሞት ለእስራት የሚያበቃው ነገር አላደረገም” ተባባሉ።

32. አግሪጳም ፊስጦስን፣ “ይህ ሰው ወደ ቄሳር ይግባኝ ባይል ኖሮ መልቀቅ ይቻል ነበር” አለው።

ሐዋርያት ሥራ 26