ሐዋርያት ሥራ 13:49-52 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

49. የጌታም ቃል በአካባቢው ባለው አገር ሁሉ ተስፋፋ።

50. አይሁድ ግን በመንፈሳዊ ነገር የተጉትንና በኑሮ የከበሩትን ሴቶች እንዲሁም የከተማውን ታላላቅ ወንዶች ቀስቅሰው በጳውሎስና በበርናባስ ላይ ስደትን አስነሡ፤ ከአገራቸውም አስወጧቸው።

51. ጳውሎስና በርናባስም ተቃውሞአቸውን ለመግለጽ የእግራቸውን ትቢያ አራግፈው ወደ ኢቆንዮን ሄዱ።

52. ደቀ መዛሙርቱም በደስታና በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ።

ሐዋርያት ሥራ 13