ሆሴዕ 12:12-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ያዕቆብ ወደ ሶርያ ሸሸ፤እስራኤል ሚስት ለማግኘት ሲል አገለገለ፤ዋጋዋንም ለመክፈል በጎችን ጠበቀ።

13. እግዚአብሔር በነቢይ አማካይነት እስራኤልን ከግብፅ አወጣ፤በነቢይም በኩል ተንከባከበው።

14. ኤፍሬም ግን ክፉኛ አስቈጣው፤ጌታውም የደም አፍሳሽነቱን በደል በላዩ ላይ ያደርግበታል፤ስለ ንቀቱም የሚገባውን ይከፍለዋል።

ሆሴዕ 12