6. በከተሞቻቸው ላይ ሰይፍ ይመዘዛል፤የበሮቻቸውን መወርወሪያ ይቈርጣል፤ስለ ክፉ ዕቅዳቸውም ይደመስሳቸዋል።
7. ሕዝቤ ከእኔ ዘወር ማለትን መረጡ፤ወደ ልዑል ቢጣሩም፣በምንም ዐይነት አያከብራቸውም።
8. “ኤፍሬም ሆይ፤ እንዴት እጥልሃለሁ?እስራኤል ሆይ፤ እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ?እንዴት እንደ አዳማ አደርግሃለሁ?እንዴትስ እንደ ሲባዮ እፈጽምብሃለሁ?ልቤ በውስጤ ተናወጠ፤ምሕረቴም ሁሉ ተነሣሥቶአል።
9. የቊጣዬን መቅሠፍት አላመጣም፤ተመልሼም ኤፍሬምን አላጠፋም፤እኔ በመካከላችሁ ያለሁ ቅዱስ አምላክ ነኝ እንጂ፣ሰው አይደለሁምና፣በቊጣ አልመጣም።
10. እግዚአብሔርን ይከተላሉ፤እርሱም እንደ አንበሳ ያገሣል፤እርሱ ሲያገሣ፣ልጆቹ እየተንቀጠቀጡ ከምዕራብ ይመጣሉ።