2 ዜና መዋዕል 22:10-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. የአካዝያስ እናት ጎቶልያ ልጇዋ መሞቱን ባየች ጊዜ፣ የይሁዳን ንጉሣውያን ቤተ ሰብ በሙሉ አጠፋች፤

11. የንጉሥ ኢዮሆራም ልጅ ዮሳቤት ግን፣ ከሚገደሉት መሳፍንት መካከል ኢዮአስን ደብቃ ወሰደችው፣ ከሞግዚቱም ጋር በእልፍኝ ሸሸገችው። የኢዮሆራም ልጅ የካህኑ የዮዳሄ ሚስት ዮሳቤት፣ የአካዝያስ እኅት በመሆኗ፣ ሕፃኑን የደበቀችው ጎቶልያ እንዳት ገድለው ነበር።

12. እርሱም ጎቶልያ ምድሪቱን በገዛችበት ጊዜ ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተደብቆ ስድስት ዓመት አብሮአቸው ኖረ።

2 ዜና መዋዕል 22