1. የክርስቶስ ኢየሱስ እስረኛ ከሆነው ከጳውሎስና ከወንድማችን ከጢሞቴዎስ፤ለውድ ወዳጃችንና አብሮን ለሚሠራው ለፊልሞና፣
2. ለእኅታችን ለአፍብያ፣ አብሮን ወታደር ለሆነው ለአርክጳ በቤትህም ላለችው ቤተ ክርስቲያን፤
3. ከእግዚአብሔር ከአባታችን፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
4. አንተን በጸሎቴ በማስብህ ጊዜ ዘወትር አምላኬን አመሰግናለሁ፤
5. ምክንያቱም በጌታ በኢየሱስ ያለህን እምነትና ለቅዱሳንም ሁሉ ያለህን ፍቅር ሰምቻለሁ።