ዳንኤል 4:35-37 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

35. የምድር ሕዝቦች ሁሉ፣እንደ ኢምንት ይቈጠራሉ፤በሰማይ ኀይላት፣በምድርም ሕዝቦች ላይ፣የወደደውን ያደርጋል፤እጁን መከልከል የሚችል የለም፤‘ምን ታደርጋለህ?’ ብሎ የሚጠይቀውም የለም።

36. አእምሮዬ እንደ ተመለሰልኝ፣ ወዲያው ለመንግሥቴ ክብር፣ ግርማዊነቴና ሞገሴ ተመለሱልኝ፤ አማካሪዎቼና መኳንንቴ ፈለጉኝ፤ ወደ ዙፋኔም ተመለስሁ፤ ከቀድሞውም የበለጠ ታላቅ ሆንሁ።

37. የሰማይ አምላክ የሚያደርገው ሁሉ ትክክል፣ መንገዶቹም ሁሉ ጽድቅ ስለሆኑ፣ አሁንም እኔ ናቡከደነፆር እርሱን አወድሰዋለሁ፤ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ፤ አከብረዋለሁም፤ እርሱም በትዕቢት የሚመላለሱትን ማዋረድ ይችላል።

ዳንኤል 4