ዳንኤል 2:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ናቡከደነፆር በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ሕልም አለመ፤ መንፈሱ ታወከ፤ እንቅልፍም ከእርሱ ራቀ።

2. ያለመውንም ሕልም እንዲነግሩት ንጉሡ ጠንቋዮችን፣ አስማተኞችን፣ መተተኞችንና ኮከብ ቈጣሪዎችን እንዲጠሩ አዘዘ፤ እነርሱም ገብተው በፊቱ ቆሙ፤

3. እርሱም፣ “አንድ ሕልም አለምሁ፤ ሕልሙም ምን እንደሆነ ለማወቅ መንፈሴ ተጨንቆአል” አላቸው።

ዳንኤል 2