ዮናስ 2:5-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ውሃ እስከ ዐንገቴ አጠለቀኝ፤ጥልቁም ከበበኝ፤የባሕርም ዐረም በራሴ ላይ ተጠመጠመ።

6. ወደ ተራሮች መሠረት ሰመጥሁ፤የምድርም በር ለዘላለም ተዘጋብኝ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤አንተ ግን ሕይወቴን ከጒድጓድ አወጣህ።

7. “ነፍሴ በዛለች ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን ዐሰብሁ፤ጸሎቴም ወደ አንተ፣ወደ ቅዱስ መቅደስህ ዐረገች።

ዮናስ 2