ዮሐንስ 19:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ጲላጦስም ኢየሱስን ወስዶ አስገረፈው።

2. ወታደሮችም የእሾህ አክሊል ጐንጒነው በራሱ ላይ አደረጉ፤ ሐምራዊ ልብስም አለበሱት፤

3. እየተመላለሱም፣ “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን” አያሉ በጥፊ ይመቱት ነበር።

4. ጲላጦስም እንደ ገና ወደ ውጭ ወጥቶ፣ “እንግዲህ ወደ እናንተ ያወጣሁት ለክስ የሚያደርስ ወንጀል እንዳላገኘሁበት እንድታውቁ ነው” አላቸው።

ዮሐንስ 19