ዮሐንስ 10:26-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

26. እናንተ ግን በጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም፤

27. በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ፤ እኔ ዐውቃቸዋለሁ፤ እነርሱም ይከተሉኛል፤

28. እኔ የዘላለም ሕይወት እሰጣቸዋለሁ፤ ከቶ አይጠፉም፤ ከእጄም ሊነጥቃቸው የሚችል ማንም የለም።

29. እነርሱን የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፤ ከአባቴም እጅ ማንም ሊነጥቃቸው አይችልም።

30. እኔና አብ አንድ ነን።”

31. አይሁድ ሊወግሩት እንደ ገና ድንጋይ አነሡ፤

ዮሐንስ 10