ዘፍጥረት 6:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሰዎች በምድር ላይ እየበዙ ሲሄዱ ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው።

2. የእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ወንዶች ልጆች የሰዎችን ሴቶች ልጆች ውብ ሆነው አዩአቸው፤ ከመካከላቸውም የመረጧቸውን አገቡ።

3. እግዚአብሔርም (ያህዌ)፣ “ሰው ሟች ስለ ሆነ መንፈሴ እያዘነ ከእርሱ ጋር ለዘላለም አይኖርም፤ ዕድሜው 120 ዓመት ይሆናል” አለ።

ዘፍጥረት 6