ዘፍጥረት 46:18-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. እነዚህ ዐሥራ ስድስት ልጆች ሁሉ፣ ላባ ለልጁ ለልያ ከሰጣት ከዘለፋ ላይ ያዕቆብ የወለዳቸው ናቸው።

19. የያዕቆብ ሚስት የራሔል ልጆች፦ዮሴፍና ብንያም ናቸው፤

20. በግብፅም የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናት፣ ምናሴንና ኤፍሬምን ለዮሴፍ ወለደችለት።

21. የብንያም ልጆች፦ቤላ፣ ቤኬር፣ አስቤል፣ ጌራ፣ ናዕማን፣አኪ፣ ሮስ፣ ማንፌንሑፊምና አርድ ናቸው።

22. እነዚህ ዐሥራ አራቱ፣ ራሔል ለያዕቆብ የወለደችለት ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው።

23. የዳን ልጅ፦ሑሺም ነው፤

24. የንፍታሌም ልጆች፦ያሕጽኤል፣ ጉኒ፣ ዬጽርና ሺሌም ናቸው፤

ዘፍጥረት 46