ዘፍጥረት 11:22-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. ሴሮሕ በ30 ዓመቱ ናኮርን ወለደ፤

23. ናኮርን ከወለደ በኋላ ሴሮሕ 200 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።

24. ናኮር በ29 ዓመቱታራን ወለደ፤

25. ታራን ከወለደ በኋላ ናኮር 119 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።

26. ታራ 70 ዓመት ከሆነው በኋላ አብራምን፣ ናኮርንና ሐራንን ወለደ።

27. የታራ ትውልድ ይህ ነው፦ታራ፣ አብራምን ናኮርንና ሐራንን ወለደ፤ሐራንም ሎጥን ወለደ።

ዘፍጥረት 11