ዘፀአት 39:41-43 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

41. በመቅደሱ ሲያገለግሉ የሚለበሱት የተፈተሉት ቀሚሶች፣ ለካህኑ ለአሮን የተቀደሱት ቀሚሶችና ወንዶች ልጆቹ ካህናት ሆነው ሲያገለግሉ የሚያደርጓቸው ቀሚሶች ናቸው።

42. እስራኤላውያን ልክ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዳዘዘው ሥራውን ሁሉ አከናወኑ።

43. ሙሴ ሥራውን አየ፤ ልክ እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘው መሥራታቸውንም ተመለከተ፤ ስለዚህ ባረካቸው።

ዘፀአት 39