23. “ምርጥ ቅመሞችን፣ አምስት መቶ ሰቅል ፈሳሽ ከርቤ፣ ግማሽ ይኸውም ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል ጣፋጭ ቀረፋ፣ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል ጠጅ ሣር፣
24. አምስት መቶ ሰቅል ብርጒድ ውሰድ፤ ሁሉም እንደ መቅደሱ ሰቅልና አንድ የኢን መስፈሪያ የወይራ ዘይት ይሁን፤
25. እነዚህን በቀማሚ እንደ ተሠራ እንደሚሸት ቅመም የተቀደሰ ቅብዐ ዘይት አድርግ፤ የተቀደሰ ቅብዐ ዘይት ይሆናል፤
26. ከዚያም የመገናኛውን ድንኳን፣ የምስክሩን ታቦት፣
27. ጠረጴዛውንና ዕቃዎቹን ሁሉ፣ መቅረዙንና ዕቃዎቹን፣ የዕጣን መሠዊያውን፣