ዘፀአት 25:5-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ቀይ የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፣ የለፋ ቆዳ፣ የግራር ዕንጨት፣

6. የመብራት ወይራ ዘይት፣ ለቅብዓ ዘይቱና ጣፋጭ መዓዛ ላለው ዕጣን የሚሆኑ ቅመሞች፣

7. በኤፉድና በደረት ኪስ ላይ የሚሆኑ መረግዶችና ሌሎች ዕንቍዎች።

8. “ከዚያም መቅደስ እንዲሠሩልኝ አድርግ፤ እኔም በመካከላቸው አድራለሁ።

9. ማደሪያ ድንኳኑንና በውስጡ ያለውን ዕቃ ሁሉ ልክ እኔ በማሳይህ ዕቅድ መሠረት ሥሩት።

ዘፀአት 25