ዘፀአት 25:37-40 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

37. “ከዚያም ሰባት መብራቶች ሠርተህ ከመቅረዙ ፊት ለፊት ለሚገኘው ስፍራ ብርሃን እንዲሰጡ ከመቅረዙ ላይ አስቀምጣቸው።

38. መኰስተሪያና የኵስታሪ ማስቀመጫ ሳህኖቹም ከንጹሕ ወርቅ ይሠሩ።

39. ለመቅረዙና ለዕቃዎቹ ሁሉ የሚያስፈልገው አንድ መክሊት ንጹሕ ወርቅ ነው።

40. በተራራው ላይ ባሳየሁህ ዕቅድ መሠረት መሥራትህን ልብ በል።

ዘፀአት 25