ዘዳግም 9:13-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ደግሞም እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዲህ አለኝ፤ “ይህን ሕዝብ አይቼዋለሁ፤ በእርግጥ ዐንገተ ደንዳና ሕዝብ ነው፣

14. አጠፋቸውና ስማቸውንም ከሰማይ በታች እደመስሰው ዘንድ ተወኝ፤ አንተንም ከእነርሱ ይልቅ ብርቱና ብዙ ሕዝብ አደርግሃለሁ።”

15. ስለዚህ ተራራው በእሳት እየተቀጣጠለ ሳለ፣ ሁለቱን የቃል ኪዳን ጽላቶች በሁለቱም እጆቼ እንደያዝሁ ከተራራው ተመልሼ ወረድሁ።

ዘዳግም 9