ዘዳግም 5:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሙሴ እስራኤልን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “እስራኤል ሆይ፤ በዛሬዋ ዕለት በጆሮአችሁ የምነግራችሁን ሥርዐትና ሕግ ስሙ፤ አጥኗቸው፤ በጥንቃቄም ጠብቋቸው።

2. አምላካችን እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በኮሬብ ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን ገብቶአል።

3. እግዚአብሔር ይህን ቃል ኪዳን የገባውም ከአባቶቻችን ጋር ሳይሆን፣ ዛሬ እዚህ በሕይወት ከምንገኘው ከእኛ ከሁላችን ጋር ነው።

ዘዳግም 5