ዘዳግም 21:5-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. እንዲያገለግሉና በእግዚአብሔር (ያህዌ) ስም እንዲባርኩ፣ በማንኛውም የክርክርና የጥቃት ጒዳዮች ሁሉ ላይ ውሳኔ እንዲሰጡ፣ አምላክህእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) መርጦአቸዋልና የሌዊ ልጆች ካህናቱ ወደ ፊት ይቅረቡ።

6. ከዚያም ሬሳው በተገኘበት አቅራቢያ ባለችው ከተማ የሚኖሩ ሽማግሌዎች ሁሉ፣ በሸለቆው ውስጥ፣ ዐንገቷ በተሰበረው ጊደር ላይ እጃቸውን ይታጠቡ።

7. እንዲህም ብለው ይናገሩ፤ “እጆቻችን ደም አላፈሰሱም፤ ድርጊቱ ሲፈጸምም ዐይኖቻችን አላዩም።

8. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ ስለ ተቤዥኸው ሕዝብህ ስለ እስራኤል ብለህ ይህን ስርየት ተቀበል፤ ሕዝብህንም በፈሰሰው ንጹሕ ደም በደለኛ አታድርግ።” ስለ ፈሰሰውም ደም ስርየት ይደረግላቸዋል።

9. አንተም በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ቀና የሆነውን ስታደርግ፣ የንጹሑን ደም የማፍሰስ በደልን ከመካከልህ ታስወግዳለህ።

ዘዳግም 21