ዘዳግም 16:19-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. ፍርድ አታዛባ፤ አድልዎ አታድርግ፤ ጒቦም አትቀበል፤ ጒቦ የጠቢባንን ዐይን ያሳውራል፤ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና።

20. በሕይወት እንድትኖርና አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የሚሰጥህን ምድር እንድትወርስ፣ ቅን ፍርድን ብቻ ተከተል።

21. ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በምትሠራው መሠዊያ አጠገብ የአሼራን ምስል የዕንጨት ዐምድ አታቁም።

ዘዳግም 16