ዘዳግም 1:10-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. አምላካችሁ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ቊጥራችሁን ጨምሮአል፤ ስለዚህ ዛሬ እናንተ እንደ ሰማይ ከዋክብት በዝታችኋል።

11. አሁንም የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ሺህ ጊዜ ያብዛችሁ፤ በሰጠውም ተስፋ መሠረት ይባርካችሁ

12. ይሁን እንጂ ችግራችሁን፣ ሸክማችሁንና ክርክራችሁን ሁሉ ብቻዬን እንዴት አድርጌ መሸከም እችላለሁ?

ዘዳግም 1