ዘካርያስ 9:3-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ጢሮስ ለራሷ ምሽግ ሠርታለች፤ብሩን እንደ ዐፈርወርቁንም እንደ መንገድ ላይ ትቢያ ቈልላለች።

4. ጌታ ግን ሀብቷን ይወስዳል፤በባሕር ያላትንም ኀይል ይደምስሳል፤እርሷም በእሳት ፈጽማ ትጠፋለች።

5. አስቀሎና አይታ ትርዳለች፤ጋዛ በሥቃይ ትቃትታለች፤አቃሮናም እንደዚሁ ትሠቃያለች፤ ተስፋዋ ይመነምናልና።ጋዛ ንጉሥዋን ታጣለች፤አስቀሎናም ባድማ ትሆናለች።

6. ድብልቅ ሕዝቦች አዛጦንን ይይዛሉ፤የፍልስጥኤማውያንንም ትምክሕት እቈርጣለሁ።

7. ደሙን ከአፋቸው፣የተከለከለውንም ምግብ ከመንጋጋቸው አወጣለሁ።የተረፉት ለአምላካችን ይሆናሉ፤በይሁዳም አለቆች ይሆናሉ፤አቃሮንም እንደ ኢያቡሳዊ ይሆናል።

8. እኔ ግን ቤቴንከዘራፊ ኀይሎች እጠብቃለሁ፤ጨቋኝ ከእንግዲህ ሕዝቤን አይወርስም፤አሁን ነቅቼ እጠብቃለሁና።

ዘካርያስ 9