ዘካርያስ 14:6-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. በዚያ ቀን በረዶ ውርጭና ብርሃን አይኖርም።

7. ቀኑም የብርሃን ወይም የጨለማ ጊዜ የሌለበት ልዩ ቀን ይሆናል፤ ያም ቀን በእግዚአብሔር የታወቀ ቀን ይሆናል፤ ሲመሽም ብርሃን ይሆናል።

8. በዚያን ቀን የሕይወት ውሃ ከኢየሩሳሌም ይፈልቃል፤ እኩሌታው ወደ ምሥራቁ ባሕር፣ እኩሌታውም ወደ ምዕራቡ ባሕር ይፈሳል፤ ይህም በበጋና በክረምት ይሆናል።

9. እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፤ በዚያን ቀን እግዚአብሔር አንድ፣ ስሙም አንድ ብቻ ይሆናል።

ዘካርያስ 14