4. ከይሁዳ፣ የማእዘን ድንጋይ፣የድንኳን ካስማ፣የጦርነት ቀስት፣ገዥም ሁሉ ይወጣል።
5. ጠላትን መንገድ ላይ እንዳለ ጭቃ ይረጋግጣሉ፤በአንድነት እንደ ጦር ሰልፈኛ ይሆናሉ፤እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ስለ ሆነ ተዋግተው፤ፈረሰኞችን ያዋርዳሉ።
6. “የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፤የዮሴፍንም ቤት እታደጋለሁ።ስለምራራላቸው፣ወደቦታቸው እመልሳቸዋለሁ፤እነርሱም በእኔ እንዳልተተዉ ሰዎችይሆናሉ፤እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር ነኝና፣ጸሎታቸውን እሰማለሁ።
7. ኤፍሬማውያን እንደ ኀያላን ሰዎች ይሆናሉ፤ልባቸውም የወይን ጠጅ እንደ ጠጣ ሰው ሐሤት ያደርጋል።ልጆቻቸው ያዩታል፤ ደስተኛም ይሆናሉ፤ልባቸውም በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል።