22. እግዚአብሔርም (ያህዌ) ሙሴን አለው፤
23. “አሮንንና ልጆቹን እንዲህ በላቸው፤ ‘እስራኤላውያንን በምትባርኩበት ጊዜ እንዲህ በሉአቸው፤
24. “ ‘እግዚአብሔር (ያህዌ) ይባርክህ፤ይጠብቅህም፤
25. እግዚአብሔር (ያህዌ) ፊቱን ያብራልህ፤ይራራልህም፤
26. እግዚአብሔር (ያህዌ) ፊቱን ይመልስልህ፤ሰላሙንም ይስጥህ።’ ”
27. “በዚህ ሁኔታ ስሜን በእስራኤላውያን ላይ ያደርጋሉ፤ እኔም እባርካቸዋለሁ።”