ዘኁልቍ 35:27-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. ደም ተበቃዩም ከከተማው ውጭ ካገኘው፣ ተከሳሹን ሊገድለው ይችላል፤ በነፍሰ ገዳይነትም አይጠየቅም።

28. ተከሳሹም ሊቀ ካህናቱ እስኪሞት ድረስ በመማጸኛው ከተማ ይቈይ፤ ወደ ገዛ ርስቱ መመለስ የሚችለው ከሊቀ ካህናቱ ሞት በኋላ ብቻ ነው።

29. “ ‘እንግዲህ በየትኛውም በምትኖሩበት ስፍራ፣ በሚመጡት ትውልዶች ሁሉ የምትፈጽሟቸው ሕጋዊ ግዴታዎቻችሁ እነዚህ ናቸው።

30. “ ‘ሰው የገደለ ማንኛውም ሰው በሞት የሚቀጣው ምስክሮች ሲመሰክሩበት ብቻ ነው፤ ይሁን እንጂ ማንም ሰው በአንድ ምስክር ብቻ በሞት አይቀጣም።

31. “ ‘በሞት መቀጣት ስላለበት ሰው የነፍስ ዋጋ አትቀበሉ፤ ፈጽሞ መሞት አለበት።

ዘኁልቍ 35