12. “ ‘በሰባተኛው ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ሥራ አትሥሩ፤ ለእግዚአብሔርም (ያህዌ) የሰባት ቀን በዓል አክብሩ።
13. ሁሉም እንከን የሌለባቸው ዐሥራ ሦስት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶች የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ እንዲያሰኝ በእሳት አቅርቡ
14. ከዐሥራ ሦስቱ ወይፈኖች ከእያንዳንዳቸው ጋር የኢፍ ሦስት ዐሥረኛ፣ ከሁለቱ አውራ በጎችም ከእያንዳንዳቸው ጋር የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የእህል ቊርባን አቅርቡ፤
15. እንዲሁም ከዐሥራ አራቱ ተባዕት የበግ ጠቦቶች ከእያንዳንዳቸው ጋር የኢፍ አንድ ዐሥረኛ በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የእህል ቊርባን አቅርቡ።
16. ከእህሉ ቊርባንና ከመጠጡ ቊርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።
17. “ ‘በሁለተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ዐሥራ ሁለት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ።