ዘኁልቍ 26:49-54 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

49. በሺሌም በኩል፣ የሺሌማውያን ጐሣ፤

50. እነዚህ የንፍታሌም ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት አርባ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።

51. ባጠቃላይ የእስራኤል ወንዶች ቍጥር ስድስት መቶ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበር።

52. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤

53. “ምድሪቱ በስማቸው ቍጥር ልክ ተደልድላ በርስትነት ለእነርሱ ትሰጥ።

54. በርከት ያለ ቊጥር ላለው ጐሣ ሰፋ ያለውን ርስት፣ አነስ ያለ ቊጥር ላለው ጐሣ ደግሞ አነስ ያለውን ስጥ፤ ርስቱንም እያንዳንዱ በዝርዝሩ ላይ በተመለከተው ቊጥር መሠረት ይረከባል።

ዘኁልቍ 26