ዘኁልቍ 23:10-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. የያዕቆብን ትቢያ ማን ቈጥሮ ይዘልቃል?የእስራኤልንስ ሩብ ማን ይቈጥረዋል።የጻድቁን ሞት እኔ ልሙት፤ፍጻሜዬም የእርሱ ዐይነት ፍጻሜ ትሁን!”

11. ባላቅም በለዓምን፣ “እንዴት እንዲህ ታደርገኛለህ? ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ አመጣሁህ፤ አንተ ግን ባረክሃቸው እንጂ ምንም አላደረግህልኝም!” አለው።

12. እርሱም መልሶ “እግዚአብሔር (ያህዌ) በአፌ ያስቀመጠውን መናገር አይገባኝምን?” አለው።

ዘኁልቍ 23