ዘኁልቍ 2:29-33 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

29. ከዚያም የንፍታሌም ነገድ ይቀጥላል፤ የንፍታሌም ሕዝብ አለቃ የዔናን ልጅ አኪሬ ሲሆን፣

30. የሰራዊቱም ብዛት አምሳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነው።

31. “በየሰራዊታቸው ሆነው ከዳን ምድብ የተመዘገቡት ወንዶች ሁሉ አንድ መቶ አምሳ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ናቸው፤ እነርሱም በዐርማቸው ሥር በመጨረሻ ይመጣሉ።

32. በየቤተ ሰባቸው፣ በየምድባቸውና በየሰራዊታቸው የተመዘገቡት እስራኤላውያን ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ናቸው፤

33. ያም ሆኖ ግን እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሌዋውያኑ ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋር አልተቈጠሩም።

ዘኁልቍ 2