6. ከካህን ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ከዚህ መብላት ይችላል፤ ነገር ግን በተቀደሰ ስፍራ ይበላ፤ ይህም እጅግ ቅዱስ ነው።
7. “ ‘የኀጢአት መሥዋዕትና የበደል መሥዋዕት አቀራረብ ሥርዐት አንድ ነው፤ መሥዋዕቶቹ የስርየቱን ሥርዐት ለሚያስ ፈጽመው ካህን ይሰጣሉ።
8. ስለማንኛውም ሰው የሚቃጠል መሥዋዕት የሚያቀርበው ካህን ቈዳውን ለራሱ ይውሰድ።
9. በማብሰያ ምድጃ የተጋገረ፣ በመቀቀያ ወይም በምጣድ የበሰለ ማንኛውም የእህል ቊርባን ለሚያቀርበው ካህን ይሰጥ።
10. ማናቸውም በዘይት የተለወሰ ወይም ደረቅ የእህል ቊርባን ለአሮን ልጆች ሁሉ እኩል ይሰጥ።