19. የትዕቢታችሁን ኀይል እሰብራለሁ፤ ሰማያችሁን እንደ ብረት፣ ምድራችሁንም እንደ ናስ አደርጋለሁ።
20. ኀይላችሁ በከንቱ ያልቃል፤ ምድራችሁ እህሏን፣ የምድሪቱ ዛፎችም ፍሬዎቻቸውን አይሰጡምና።
21. “ ‘በእኔ ላይ ማመፅ ብትቀጥሉና ባትታዘዙኝ እንደ ኀጢአታችሁ መጠን ሰባት ዕጥፍ መቅሠፍት እጨምርባችኋለሁ።
22. የዱር አራዊትን እሰድባችኋለሁ፤ ልጆቻችሁን ይነጥቋችኋል፤ ከብቶቻችሁን ያጠፉባችኋል፤ ቊጥራችሁ ይመነምናል፤ መንገዶቻችሁም ሰው አልባ ይሆናሉ።
23. “ ‘በዚህ ሁሉ ግን ወደ እኔ ባትመለሱ፣ በእኔም ላይ ማመፃችሁን ብትቀጥሉ
24. እኔም ጠላት እሆንባችኋለሁ፤ ስለ ኀጢአታችሁም ሰባት ዕጥፍ አስጨንቃችኋለሁ።