ዘሌዋውያን 23:5-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት የእግዚአብሔር (ያህዌ) ፋሲካ በዓል ይጀመራል።

6. በዚያው ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን የእግዚአብሔር (ያህዌ) የቂጣ በዓል ይጀመራል፤ ሰባት ቀንም ያለ እርሾ የተጋገረ ቂጣ ትበላላችሁ።

7. በመጀመሪያው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዕለት ተግባራችሁንም አታከናውኑ።

8. ሰባት ቀን በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) አቅርቡ፤ በሰባተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ በዚያ ዕለት የተለመደ ተግባራችሁን አታከናውኑ።’ ”

ዘሌዋውያን 23