ዘሌዋውያን 21:12-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. የተቀደሰበት የአምላኩ (ኤሎሂም) የቅባት ዘይት በላዩ ስለ ሆነ የአምላኩን (ኤሎሂም) መቅደስ ትቶ በመሄድ መቅደሱን አያርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።

13. “ ‘ካህኑ የሚያገባት ሴት ድንግል ትሁን።

14. ባል የሞተባትን፣ የተፋታችውን ወይም በዝሙት ዐዳሪነት የረከሰችውን ሴት አያግባ፤ ነገር ግን ከወገኖቹ መካከል ድንግሊቱን ያግባ።

15. በወገኖቹ መካከል ዘሩን አያርክስ። እርሱን የምቀድሰው እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።’ ”

16. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤

ዘሌዋውያን 21