ዘሌዋውያን 2:14-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. “ ‘የእህል በኵራት ቊርባን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በምታመጣበት ጊዜ፣ የተፈተገና በእሳት የተጠበሰ እሸት አቅርብ።

15. ዘይት ጨምርበት፤ ዕጣንም በላዩ አስቀምጥ፤ ይህ የእህል ቊርባን ነው።

16. ካህኑም ከተፈተገው እህልና ከዘይቱ ወስዶ፣ ከዕጣኑ ሁሉ ጋር ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት የሚቀርብ መታሰቢያ አድርጎ ያቃጥል።

ዘሌዋውያን 2