ዘሌዋውያን 18:24-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

24. “ ‘ከእነዚህ በአንዱ እንኳን ራሳችሁን አታርክሱ፤ ከፊታችሁ የማሳድዳቸው አሕዛብ በእነዚህ ሁሉ ረክሰዋልና።

25. ምድሪቱም ሳትቀር ረከሰች፤ እኔም ስለ ኀጢአቷ ቀጣኋት፤ ስለዚህ የሚኖሩባትን ሰዎች ተፋቻቸው።

26. እናንተ ግን ሥርዐቴንና ሕጌን ጠብቁ፤ እናንተ የአገር ተወላጆችና በመካከላችሁ የሚኖሩ መጻተኞች ከእነዚህ አስጸያፊ ድርጊቶች ማንኛውንም አትፈጽሙ።

27. ከእናንተ በፊት በምድሪቱ የኖሩ ሰዎች እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ ስለ ፈጸሙ፣ ምድሪቱ ረክሳለች።

ዘሌዋውያን 18