ዕብራውያን 8:8-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ነገር ግን እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ጒድለት በማግኘቱ እንዲህ ይላቸዋል፤“ከእስራኤል ቤት ጋር፣ከይሁዳም ቤት ጋር፣አዲስ ኪዳን የምገባበት፣ጊዜ ይመጣል፤ ይላል ጌታ።

9. ይህም እነርሱን ከግብፅ ምድርለማውጣት እጃቸውን በያዝሁ ጊዜ፣ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ኪዳን አይደለም፤ምክንያቱም እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑም፤እኔም ከእነርሱ ዘወር አልሁ፤ይላል ጌታ።

10. ከዚያን ጊዜ በኋላ፣ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው፤ ይላል ጌታ፤ሕጌን በአእምሮአችው አኖራለሁ፤በልባቸውም እጽፈዋለሁ።እኔ አምላካቸው እሆናለሁ፤እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።

ዕብራውያን 8