10. ከዚያን ጊዜ በኋላ፣ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው፤ ይላል ጌታ፤ሕጌን በአእምሮአችው አኖራለሁ፤በልባቸውም እጽፈዋለሁ።እኔ አምላካቸው እሆናለሁ፤እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።
11. ከእንግዲህ ማንም ሰው ጐረቤቱንወይም ወንድሙን፣ ‘ጌታን ዕወቅ’ ብሎ አያስተምርም፤ምክንያቱም ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ፣ሁሉም ያውቁኛል።
12. በደላቸውን ይቅር እላለሁ፤ ኀጢአታቸውንከእንግዲህ አላስብም።”
13. ይህን ኪዳን፣ “አዲስ” በማለቱ የፊተኛውን ኪዳን አሮጌ አድርጎታል፤ ስለዚህ ያረጀ ያፈጀው የሚጠፋበት ጊዜ ተቃርቦአል።