ዕብራውያን 3:17-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. አርባ ዓመት የተቈጣውስ እነማንን ነበር? ኀጢአት ሠርተው ሬሳቸው በምድረ በዳ ወድቆ የቀረውን አይደለምን?

18. ያልታዘዙትን ካልሆነ በቀር ወደ ዕረፍቱ እንዳይገቡ የማለባቸው እነማን ነበሩ?

19. እንግዲህ ሊገቡ ያልቻሉት ካለማመናቸው የተነሣ እንደሆነ እንረዳለን።

ዕብራውያን 3