ኤርምያስ 52:32-34 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

32. በመልካምም ቃል አናገረው፤ ከእርሱም ጋር በባቢሎን በምርኮ ከነበሩት ነገሥታት ይልቅ ከፍ ባለ የክብር ቦታ አስቀመጠው።

33. ዮአኪንም እስር ቤት ለብሶት የነበረውን ልብሱን አውልቆ ጣለ፤ በቀረውም የሕይወቱ ዘመን ሁሉ ከንጉሡ ማእድ ይበላ ነበር።

34. የባቢሎንም ንጉሥ፣ ዮአኪን እስኪሞት ድረስ፣ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሳያቋርጥ በየዕለቱ ቀለቡን ይሰጠው ነበር።

ኤርምያስ 52