ኤርምያስ 51:47-50 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

47. የባቢሎንን ጣዖታት የምቀጣበት ጊዜ፣በርግጥ ይመጣልና።ምድሯ በሙሉ ትዋረዳለች፤የታረዱትም በሙሉ በውስጧ ይወድቃሉ።

48. ሰማይና ምድር በውስጣቸውም ያለው ሁሉ፣በባቢሎን ላይ እልል ይላሉ፤አጥፊዎች ከሰሜን ወጥተው፣እርሷን ይወጓታልና፤”ይላል እግዚአብሔር።

49. “በምድር ሁሉ የታረዱት፣በባቢሎን ምክንያት እንደ ወደቁ፣ባቢሎንም በእስራኤል በታረዱት ምክንያት መውደቅ ይገባታል።

50. ከሰይፍ ያመለጣችሁ ሆይ፤ሂዱ! ጊዜ አትፍጁ፤በሩቅ ምድር ያላችሁ እግዚአብሔርን አስታውሱ፤ኢየሩሳሌምንም አስቧት።”

ኤርምያስ 51