ኤርምያስ 51:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እነሆ፤ በባቢሎንና በምድሯ ላይ፣የሚያጠፋ ነፋስ አስነሣለሁ።

2. እንዲያበጥሯትና እንዲያወድሟት፣ባዕዳንን በባቢሎን ላይ እልካለሁ፤በመከራዋም ቀን፣ከበው ያስጨንቋታል።

3. ቀስተኛው ቀስቱን እስኪገትር፣የጦር ልብሱንም እስኪለብስ ፋታ አትስጡት፤ለወጣቶቿ አትዘኑ፤ሰራዊቷንም ፈጽማችሁ አጥፉ።

4. በባቢሎን ምድር ታርደው፣በአደባባዮቿም እስከ ሞት ቈስለው ይወድቃሉ።

ኤርምያስ 51