ኤርምያስ 50:35-37 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

35. “ሰይፍ በባቢሎናውያን ላይ መጣ!”ይላል እግዚአብሔር፤“በባቢሎን ነዋሪዎች ላይ፤በባለ ሥልጣኖቿና በጥበበኞቿም ላይ ተመዘዘ!

36. ሰይፍ በሐሰተኞች ነቢያቷ ላይ መጣ!እነርሱም ሞኞች ይሆናሉ፤ሰይፍ በጦረኞቿ ላይ ተመዘዘ፤እነርሱም ይሸበራሉ።

37. ሰይፍ በፈረሰኞቿና በሠረገሎቿ ላይ፣በመካከሏ ባሉት ባዕዳን ወታደሮች ሁሉ ላይ መጣ!እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ፤ሰይፍ በሀብት ንብረቷ ላይ መጣ!ለዝርፊያም ይሆናሉ።

ኤርምያስ 50